ግጭት ከተቀሰቀሰባት ሞያሌ ወደ ኬንያ ድንበር "ሮኬቶች መተኮሳቸውን" የኬንያ ፖሊስ አስታወቀ - BBC News አማርኛ
ሁለተኛ ሳምንቱን በያዘው የሞያሌ ግጭት ሦስት "አርፒጂ የጦር መሣሪያዎች" ከኢትዮጵያ ድንበር ወደ ኬንያ ድንበር መተኮሳቸውን የኬንያ ፖሊስ ባለሥልጣን ለቢቢሲ ገለጹ። የሞያሌ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ጆርጅ ኪፕኮሮስ፤ ትናንት እሑድ ጥቅምት 22/2019 ዓ. ም. ሮኬቶቹ መተኮሳቸውን አረጋግጠዋል። እስከ አሁን ድረስ ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል በጉዳዩ ላይ ምንም ዓይነት አስተያየት አልተሰጠም።
Read more











